ቢሮው ያለፉት 5 ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሂዷል። ትራንስፖርት ቢሮ ግንቦት 10/ 2018ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በዘርፉ የተከናወኑ 5 ዓመት ተግባራት አፈጻጸም መነሻ ያደረገ ውይይት ያከናወነ ሲሆን በዋናነት በትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፣ በትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ፣ በዘርፍ አቅም ግንባታ እና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በገቢ አሰባሳብ እና የስራ እድል ፈጠራን ላይ የተሰሩ ስራዎች በዝርዘር በሪፖርት ቀርቦ ተገምግማል፡፡ ቢሮው ወደ ዘላቂ ትራንስፖርት (Sustainable Transport) ለመሸጋገር በዋናነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማስፋፈትና መሠረተ ልማቶችን በበቂ ሁኔታ የማሟላትና የአካባቢ ብክለትን መቆጣጠር ተሰሩ ስራዎች፣ የብዙሃን ትራንስፖርትን አቅርቦት ማሳደግ ፣ የሞተር አልባ ትራንስፖርት ማስፋፋት እና በኮሊደር ልማት የለሙ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ ከመጠቀም እና ለታለመለት አገልግሎት እንዲውሉ ማድረግ እና የዘርፉ አገልግሎት አሰጣት መሻሻሉን የቢሮው ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ የገለጹ ሲሆን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስራዎች ማሳደግ፣ የዘርፉ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ የግልና መንግስት አጋርነት ማጠናከር አንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርት አማጮችን እና አቅርቦትን ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ በመጨረሻ ሪፖርት መነሻ በማድረግ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ተግባረት ታሳቢ ያደረገ አቅድ የማዘጋጀት ስራ አንዲሰራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል። ፈስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb በቴሌግራም https://t.me/transport_bureau በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@Addisababatransportbureau በሊንክድ ኢን https://www.linkedin.com/ Addisababatransportbureau በቲክቶክ@addisababatransportbureau